በመንግስትና በመንግስት በሚደገፉ ኃይሎች በኦሮሚያ ክልል የሚፈፀሙ የንፁሃን ዜጎች ግድያ ሊቆም ይገባል፡፡

በመንግስትና በመንግስት በሚደገፉ ኃይሎች በኦሮሚያ ክልል የሚፈፀሙ የንፁሃን ዜጎች ግድያ ሊቆም ይገባል፡፡

በመንግስትና በመንግስት በሚደገፉ ኃይሎች በኦሮሚያ ክልል የሚፈፀሙ የንፁሃን ዜጎች ግድያ ሊቆም ይገባል፡፡

በኦሮሚያ ክልል እየተባባሰ የመጣውን የሰላማዊ ዜጎች ግድያ በመቃወም ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) የተሰጠ መግለጫ

በኢትዮጵያ የአምባገኑን የኢህአዴግ መንግሰት ለመገርሰስ የተካሄደው ህዝባዊ ትግል ተጠልፎና ወደ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የሚደረገው የሽግግር ሂደት ከተደናቀፈ ወዲህ የፖለቲካ ልዩነቶች ሰፍተው በሺህ የሚቆጠሩ ንፁሃን ሞት ምክንያት ከሆነ ሰንብቷል። ኦፌኮም ኃላፊነት እንደሚሰማው የፖለቲካ ፓርቲ የሃገሪቱ ፖለቲካ ከጠመንጃ አፍ ወጥቶ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ፖለቲካ እንዲለወጥ ባገኘው መድረክ ሁሉ ሲጠይቅ ቆይቷል። ነገር ግን ሰሚ ጆሮ ባለማግኘታችን በኦሮሚያ ክልል ያለው ጦርነት ተባብሶ የኦሮሞ ህዝብ በጦር አይሮፕላኖችና ተዋጊ ድሮኖች ጭምር ቄዔው እየተቃጠለና ልጆቹም በጥይት አረር እየረገፉ ይገኛሉ።

ገዢው ኃይል የፖለቲካ ቀውሱን መፍታት ባለመቻሉ ምክንያት የታጠቁ ኃይሎቹ ንፁሃንን ዜጎችን እየገደሉ፣ ቤትና እህል እያቃጠሉና እያፈናቀሉ ዘግናኝ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ። ይህም አልበቃ ብሎ ፋኖ የተባለ የአማራ ፅንፈኛ ኃይልን ጨምሮ የተለያዩ የታጠቁ ኢመደበኛ ኃይሎችን በኦሮሚያና ከኦሮሚያ ውጪ በማደራጀት እና በመደገፍ በፀረ አማፂ እንቅስቃሴ ስም በሰላማዊ ዜጎች ግድያ ላይ በስፋት እንዲሰማሩ ተደርገዋል። በአጠቃላይ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሰፊ ጥቃት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እየደረሰ መሆኑን ተረድተናል፡፡

በተለይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ፅንፈኛውን የአማራ ታጣቂ ፋኖን ጨምሮ በመንግሰት የታጠቁ ኃይሎች በንፁሃን ላይ የሚፈፀሙ ቀጥተኛ ጥቃቶች ተባብሰዋል። በጥቅምት ወር የመጀመሪያ 14 ቀናት ውስጥ ብቻ በድምሩ ከ120 በላይ ንፁሃን ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል።

ጥቅምት 5/2015 ዓም በመንግስት የሚደገፈው ፅንፈኛው የአማራ ፋኖ ኃይል በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ 30 ሰላማዊ ኦሮሞዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል። በተመሳሳይ ይሄው ፅንፈኛ ኃይል ጥቅምት 9/2015 ዓም በምስራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ 8 ንፁሃን ኦሮሞችን በአሰቃቂ መንገድ ገድሏል። ከነሱም መካከል አቶ ካሳሁን አዳነ የሚባሉ ዳቦ በመሸጥ የሚታዳደሩ ሰላማዊ ሰው አንገታቸውን በካራ በማረድ በጭካኔ የተገደሉ ይገኙበታል። ይህ ግድያ የተፈጸመ ዕለት በአካባቢው የነበሩት የመንግስት ኃይሎች እንዲደርሱላቸው ያቀረቡት ዋይታ ሰሚ አላገኘም። በዚያኑ ጊዜ ተጎጂዎች ህይወታቸውን እንዲያተርፍ በአቅራቢያው በሚገኘው የኩምሳ ሞሮዳ ቤተ መንግስት ሰፍሮ ለሚገኘው የሃገር መከላከያ ሰራዊት አቤት ለማለት ተሰባስበው ሲሄዱ የጥይት እሩምታ በመተኮስ እንዲበተኑ ተደርጓል።

በጥቅምት 9/2015 ዓም በምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወልቂጤ ወረዳ በምትገኘው ቀሬ ሄጦ ቀበሌ በመንግሰት ኃይሎች በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ህፃናት፣ ሴቶችና አዛውንቶችን ጨምሮ 14 ንፁሃን ዜጎች ተገድለዋል። በዚህ ጥቃት በርካታ የመኖሪያ ቤቶችና አንድ ትምህርት ቤት ወድሟል። በተመሳሳይ ሁኔታ በጥቅምት 12/2015 ዓም በምስራቅ ወለጋ ዞን ዋማ አገሎ ወረዳ፣ እንዲሁም ጥቅምት 13/2015 ዓም በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ በሚግ 29 የጦር አውሮፕላኖች በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ንፁሃን ተገድለዋል።

በሌላ በኩል ጥቅምት 13/2015 ዓም በምዕራብ ሸዋ ዞን ጮቢ ወረዳ በኬ ኦፉ በተባለ ቀበሌ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ በመንግሰት ኃይሎች በድሮን በተፈፀመ ጥቃት የ7 እና 10 አመት እድሜ ያላቸው ህፃናት፣ አራስ እናቶች፣ አዛውንቶች እና አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ 38 ንፁሃን ተገድለዋል። አራስ የነበረችው አለሚቱ ጃጋማ፣የ10 አመት ህፃን የሆነችው ቀበኔ ተስፋዬ፣እንዲሁም መስማት የተሳነው ቱጃራ ደበላ ጀቤሳ የተባሉት ንፁሃን በእርሻ ቦታቸው በቆሎ ምርት በሚሰበስቡበት ወቅት በጭካኔ የጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት መሃል ይገኛሉ።

በአጠቃላይ የመንግስትን ስልጣን የተቆጣጠረው ኃይል የሰላማዊ ዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ከመሳን ባለፈ፣ በራሱ እና በሱ ድጋፈ ከሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች ጋር በመሆን ድሮንና የጦር አይሮፕላኖችን በመጠቀም የሰላማዊ ዜጎች ግድያ ላይ ተሰማርቷል። በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚፈፀሙት ግድያዎችና ግፎች ህዝብ እንዳያውቀውና መረጃ ታፍኖ እንዲቀር በተቀናጀ መንገድ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ይህ ደግሞ በአለም አቀፍ ህግ የተከለከለ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል ነው።

ስለዚህ:-

1/ ሃገር አስተዳደርለለሁ በሚለው ኃይል በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ የአለምአቀፉ ማህበረሰብ እንዲገነዘብና ትኩረት እንዲሰጠው፣

2/ የአለም አቀፍ ሚዲያዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡት እንጠይቃለን፣

3/ የተባበሩት መንግስታት፣በተለይም የፀጥታው ም/ቤት በዚህ ጉዳይ ላይ በአፋጣኝ ተወያይቶ እነዚህ ግድያዎች በገለልተኛ አካላት እንዲጣሩና፣ በዚህ የሰብዓዊነት መብት ጥሰት ላይ የተሰማሩ ኃይሎች በህግ እንዲጠየቁ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ እንጠይቃለን፣

4/ የሃገር ወስጥና የውጪ ሲቪክ ማሀረበራት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ሚዲያዎች ይህን ግፍ በማጋለጥ ለህዝባቸው ድምፅ እንዲሆኑ እንጠይቃለን፣

5/ የኦሮሞ ህዝብ የተደቀነበትን ሁለንትናዊ አደጋ በመረዳት መብቱን ለማስከበር የሚያካሂደውን ትግል ከመሪ ድርጅቱ ጎን በመሰለፍ እንዲያፋፍም ጥሪ እናቀረረባለን፣

6/ በእርስ በርስ ጦርነቱ እየተሳተፉ ያሉ ኃይሎች በሙሉ የሰላማዊ ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ ካለው እንቅስቃሴ በመታቀብ ወደ ድርድርና እርቅ መድረክ እንዲመለሱ በድጋሜ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)

ፊንፊኔ፤ ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓም

SBO
ADMINISTRATOR
PROFILE

Posts Carousel

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

Latest Posts

Top Authors

  • SBO
    ADMINISTRATOR

Most Commented

Featured Videos

Categories

SBO