በኦሮሚያ ዜጎች ላይ እልቂት እንዲፈጸም ጥሪ በማቅረብ ላይ የሚገኙ ቡድኖችና ኣካላት ተጠያቂዎች ናቸው

በኦሮሚያ ዜጎች ላይ እልቂት እንዲፈጸም ጥሪ በማቅረብ ላይ የሚገኙ ቡድኖችና ኣካላት ተጠያቂዎች ናቸው

ኦሮሞን ከደመኛ ጠላቱ በመቁጠር ከኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት በተጻራሪ የሚሰራው ይህ በፖለቲካ ድርጅት ስም እየተንቀሳቀሰ ያለው ባለስልጣን ከድርጊቱ እንዲቆጠብ እንጠይቃለን።

በኦሮሚያ ዜጎች ላይ እልቂት እንዲፈጸም ጥሪ በማቅረብ ላይ የሚገኙ ቡድኖችና ኣካላት ተጠያቂዎች ናቸው

የኦነግ ርዕሰ-ኣንቀጽ -ህዳር 26 ቀን 2022ዓም

“ዓሣን ለማስፋፋት ባሕሩን ማድረቅ” በሚል ስም በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደረገው ውጊያና እልቂት እንዲቀጥል የብልጽግና ባለሥልጣን ኣቶ ፍቃዱ ተሰማ ያቀረበው ጥሪ፣ ሰኔ 28ቀን 2022ዓም “ሽምቅ ተዋጊ ኃይሎችን በጋራ ማስወገድ” በሚል ስም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ኣቶ ሽመልስ ኣብዲሳና የኣማራ ክልል ፕሬዝዳንት ኣቶ ይልቃል ከፋለ በመገናኛ ብዙሃን ወጥተው የዘር ማጥፋት ጥሪ አወጁ።

በዚህም በብልጽግና ፓርቲ መንግስት ኣቀናጅነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ቤትና ንብረት ወድሟል፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት በቀዬአቸው ተፈናቅለዋል።

ለዘመናት የኦሮሞን ህዝብ ፍላጎት ለመስበርና የኦሮሞን የነጻነት ትግል ጎራ መናድ እንደስትራተጂ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ አካላት፡ ኦሮሚያ ዜጎች ላይ ላወጁት የዘር ማጥፋት ወንጀል ጥሪ ከወንጀሉ ፈጻሚዎች ጋር ሃላፊነቱን ሊወስዱ ይገባል።

የኣምባገነኑን የብልጽግና መንግስት ጋዳ ተሸሽጎ፣ ከስርዓቱ የተሰጠውን ስልጣን በመጠቀም፣ ለዘመናት የኦሮሞን ህዝብ ፍላጎት በመጻረር ሲሰራ የቆየውና “ የኦሮሞ ህዝብ ትግል ስላሰጋኝ ነው ወደ ትግል የገባሁት” የሚለው የኢዜማ ፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና ተከታዮቹ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃንና ህዝባዊ መድረኮች ላይ “ሸኔን ማጥፋት” በሚል ስም በኦሮሚያ ዜጎች ላይ የዘር-ማጥፋት ዘመቻ በማወጅ ላይ እንደሚገኙ በግልጽ ይታያል።

ኦሮሞን ከደመኛ ጠላቱ በመቁጠር ከኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት በተጻራሪ የሚሰራው ይህ በፖለቲካ ድርጅት ስም እየተንቀሳቀሰ ያለው ባለስልጣን ከድርጊቱ እንዲቆጠብ እንጠይቃለን።

ከዚህ ቀደም ከኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግልና ከኦሮሞ ታጋዮች ያለውን ስጋት በተለያዩ ጽሁፎች በማቅረብና የስም ማጥፋት ድርጊቶችን ሲፈጽም እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬ ላገኙት ስልጣን በሩን የከፈተው የኦሮሞ ትግል መሆኑ መዘንጋት የለበትም።

የኦሮሞ ህዝብ የዘመናት ፍላጎትና ምኞቱ ለሆነው ለነጻነቱና ለሃገሩ ሉዓላዊነት መሳካት ለዝመናት ትግል እያካሄደ ይገኛል። የኦሮሞ ወጣቶች(ቄሮ) እና በአጠቃላይ የኦሮሞ ህዝብ በመላው ኦሮሚያ ውስጥ ደሙን ኣፍስሶ ኣምባገነኑን የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግስት ቢያስወግድም፡ የቄሮ ድል በመጠለፉ የኦሮሞ ወጣቶች(ቄሮም) የኦሮሞ ህዝብም የነጻነት ትግሉን ቀጥለዋል።

የኦሮሞ ህዝብ ትግሉን ኣጠናክሮ መቀጠል፡ የሌሎችን ህዝቦች እጣ ፈንታ ለማፈን እንዳልሆነ ለዓመታት ባካሄደውና እያካሄደም ባለው ትግል በመሬት ላይ በተግባር አስመስክሯል።

ትናንትም ሆነ ዛሬ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብቱንና ነጻነቱን እውን ለማድረግ ካለው ፍላጎት እንጂ፡ የኦሮሞ ህዝብ የነጻነት ትግል ጥላቶች እንደሚሉት አለመሆኑን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አጥብቆ ያሳስባል።

በመጨረሻም በኦሮሚያ ውስጥ እየተካሄደ ላለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጨማሪ የእልቂት ጥሪ በማቅረብ ላይ የሚገኑት የብልጽግና መንግስትም ሆነ ድርጅትና ግለሰቦች በሃገሪቷና በኣለምአቀፍ ህጎች መሰረት ባለፉት ዓመታት ለደረሰውና እየደረሰ ላለው እልቂት ተጠያቂነት እንዳለባቸው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) ያሳስባል። የኦሮሞ ህዝብ ጥላቻና ጦርነትን በማባባስ ላይ የሚገኑኙትን ሁሉ ለመከላከል ክንዱን ኣጠናክሮ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ እያካሄደ ባለው ትግል ላይ እንዲያተኩርም ባሳሰብ እንወዳለን።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ ሲያቀርብ እንደነበረው ግድያን፣ ጦርነትን ለማስፋትና ሰላምን ለማደናቀፍ እየተፈጸመ ያለውን ድርጊት ለማስቆም ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት በድጋሚ ጥሪ እያቀረብን፣ ለኢትዮጵያ ኢምፓየር የፖለቲካ ችግሮች ሁሉን-አቀፍ የፖለቲካ ውይይት እውን ለማድረግ ሁሉም መስራት አለበት እንላለን።

ድል ለሰፊው ህዝብ!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር

ሕዳር 26 ቀን 2022ዓም

ፊንፊኔ፡ ኦሮሚያ

SBO
ADMINISTRATOR
PROFILE

Posts Carousel

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

Latest Posts

Top Authors

  • SBO
    ADMINISTRATOR

Most Commented

Featured Videos

Categories

SBO