የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በቸልተኝነትና ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በሰላማዊ ሰዎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ወንጀል አጥብቆ አወግዛል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በቸልተኝነትና ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በሰላማዊ ሰዎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ወንጀል አጥብቆ አወግዛል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በመጨረሻም የብልጽግና መንግስት በሰላማዊ ህዝብ ላይ የቦምብ ናዳ ማዝነቡንና በጦር ሃይሉ በኦሮሚያ ዜጎች ላይ የጅምላ እልቂት መፈጸሙን እንዲገታ፡ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ሁሉም ሰላም ወዳዶች የበኩላቸውን ጫና እንዲያሳድሩ በድጋሚ ይጠይቃል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በቸልተኝነትና ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በሰላማዊ ሰዎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ወንጀል አጥብቆ አወግዛል።

የኦነግ ርዕሰ-ኣንቀጽ – ታህሳስ 03,2022ዓም

የብልጽግና ፓርቲ መንግስት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ቦምብ ማዝነብና በእግረኛ ጦር ኃይሎች አሰቃቂ ግድያ ማድረሱን ቀጥሏል። ከጥቅምት ወር አጋማሽ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ማጥፋት በሚል ዘመቻ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች እየፈጸመ ባለው የአየር ድብደባ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎችን ህይወት ቀጥፏል።

ዛሬም ጥረው ግረብ በላባቸው ኑሮኣቸውን የሚመሩ፣ ከሥራቸው በስተቀር ኣንዳችም የጦር መሳሪያ የሌላቸውን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመኖሪያ ቤትና በእርሻ ማሳ ውስጥ፡ በአምልኮ ቦታዎች፣ በመሰብሰቢያ ቦታዎች፣ በትምህርት ቤቶች፡ ወዘተ ከሰማይ በተጣለባቸው ቦምብ እየተገደሉ ይገኛሉ።

እ.ኤ.አ. ታህሳስ 02 ቀን 2022ዓም፥ በትላንትናው ዕለት፡ በማዕከላዊ ኦሮሚያ ሰሜን ሸገር ዞን ወረ-ጃርሶና ኩዩ ወረዳዎች ውስጥ የአገዛዙ የጦር አውሮፕላኖች የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ማጥቃት በሚል በተደጋጋሚ በህዝቡ ቀዬ ላይ ባደረሱት ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውና በርካቶች መቁሰላቸውን ከህዝቡ የተገኘ ተጨባጭ መረጃ ኢፋ ያደርጋል ።

በወረ-ጃርሶ ወረዳ ፋጂ ኤጄርሳ በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ ላይ በደረሰ የአየር ጥቃት የበርካታ ንፁሃን ዜጎች ህይወት አልፏል። እንደዘገባው ከሆነ ቢያንስ 80 ሰዎች ሞተዋል፡ ብዙዎች ቆስለዋል። የአንድ ቤተሰብ ኣባላት የሆኑ 6 ሰዎች በአንድ ጊዜ መገደላቸውም ተሰምቷል። እነዚህ በብልጽግና መንግስት የጦር ኣውሮፕላን ቦምብ የተገደሉት ሰላማዊ ሰዎች ለዕለት ስራቸው ከቤት የወጡ፣ ኣርሶ ኣደሮች፣ ከትምህርት ቤት በመመለስ ላይ የነበሩ ተማሪዎችና ወደ ለቅሶ ቤት በመሄድ ላይ የነበሩ ሰላማዊ ዜጎች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል። በጥቃቱ ቆስለው ለአካል ጉዳተኝነት የተጋለጡትም በቁጥር ኣያሌ ናቸው።

በኩዩ ወረዳ ላይ የተፈጸመው የአየር ድብደባም መጠነ-ሰፊ፡ ብዙ ሰዎች የተገደሉበትና የቆሰሉበት እንደሆነ ከህዝቡ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። የብልጽግና መንግስት ወታደራዊ አውሮፕላኖች(ሚግ) በኩዩ ኡዬ ጨበሬና ቀሬ ታኣ ቀበሌዎች ላይ (4)ኣራት ጊዜ ቦምብ ኣዝንበዋል። የጥቃቱ መጠን አንድን መንደር ሙሉ በሙሉ የሚያወድም እንደሆነ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

የደረሰው ጉዳት በውል ባይታወቅም ታህሳስ 01 ቀን 2022ዓም የብልጽግና መንግስት በምዕራብ ኦሮሚያ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጉዱሩ ገበቴ ላይ የአየር ላይ ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎች ገልጸዋል። መስመሩ የተዘጋ በመሆኑ የደረሰውን ጉዳት ለመረዳት አስቸጋሪ ቢሆንም አሰቃቂና መጠነ-ሰፊ እንደሆነ ይነገራል።

የብልጽግና ፓርቲ መንግስት ከአየር ጥቃቱም በተጨማሪ በምስራቅ ወለጋና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች ውስጥ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖ ህዝቡ በሰላም ሰርቶ እንዳይኖር በማድረግ፡ በየቀኑ በኦሮሞ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ መፈጸሙን፡ በሺዎች የሚቆጠሩት ከቀዬኣቸው እንዲፈናቀሉ፣ የህዝቡ ቤትና ንብረት እንዲወድም ማድረጉን ቀጥሎበታል።

የፋኖ አሸባሪ ቡድን፣ የአማራ ክልል ሚሊሻ/ልዩ ሃይል እና የመከላከያ ሰራዊት በተለያዩ ዘዴዎችና ስልቶች በጋራ ባበጁት ቅንጅት በምስራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች ውስጥ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የጦር ወንጀል መፈጸማቸውን ቀጥለዋል። የሩቁን ትተን መጋቢት 29 ቀን 2022ዓም በኪረሙ የተፈፀመው የጅምላ እልቂት ለዚህ ትልቅ ማሳያ ነው።

በአጠቃላይ በብልጽግና ፓርቲ የሚመራው የፌዴራል መንግስት የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ማጥፋት በሚል ሽፋን ሰላማዊ ዜጎችን በየቤታቸው በተዋጊ ጄቶች እና እግረኛ ጦር ሃይል መግደሉን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እንደካሁን ቀደሙ ኣሁንም ኣጥብቆ ያወግዛል፥ ለህዝቡም ያሳውቃል። ይህ መንግስት የተያያዘው እገዛዋለሁ የሚለውን ህዝብ ደም የማፍሰስ መንገድ የሚያስጠይቀው ወንጀል መሆኑንም ኦነግ ያሳስባል። የፖለቲካ ችግርን በወታደራዊ ሃይል ለመፍታት በመሞከር ሰላማዊውን ህዝብ በቦምብ መደብደብ ቀውሱን ከማባባስ ውጪ የሚመጣው ኣንዳችም መፍትሄ ኣለመኖሩ ዛሬም የኦነግ የጸና ኣቋም ነው።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በመጨረሻም የብልጽግና መንግስት በሰላማዊ ህዝብ ላይ የቦምብ ናዳ ማዝነቡንና በጦር ሃይሉ በኦሮሚያ ዜጎች ላይ የጅምላ እልቂት መፈጸሙን እንዲገታ፡ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ሁሉም ሰላም ወዳዶች የበኩላቸውን ጫና እንዲያሳድሩ በድጋሚ ይጠይቃል።

ድል ለሰፊው ህዝብ!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር

ታህሳስ 03 ቀን 2022ዓም

ፊንፊኔ

SBO
ADMINISTRATOR
PROFILE

Posts Carousel

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

Latest Posts

Top Authors

  • SBO
    ADMINISTRATOR

Most Commented

Featured Videos

Categories

SBO