የኦሮሞ ነፃነት ግንባር 50ኛ ኢዮቤልዩ የምስረታ በዓል

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር 50ኛ ኢዮቤልዩ የምስረታ በዓል

ሰማዕቶቻችንን እናስብ፣ ስኬቶቻችንን እናክብር እናም የወደፊት አቅጣጫዎቻችንን እናስቀምጥ

ሰማዕቶቻችንን እናስብ፣ ስኬቶቻችንን እናክብር እናም የወደፊት አቅጣጫዎቻችንን እናስቀምጥ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ለኦሮሞ ህዝብ እና ለኦሮሚያ ዜጎች የጋራ እና የግለሰብ መብት መከበር የሚታገል በመሆኑ የፖለቲካ መብትን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ግንባር ነው። የማይናወጥ እና ሁሌም የሚያብረቀርቅ የፖለቲካ አላማው የኦሮሞ ህዝብ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ማረጋገጥ፣መጠበቅ እና መከላከል ነው። ኦነግ ህዝቡን በአለም አቀፍ ደረጃ የተረጋግጠና ተቀባይነት ያለው የጋራ መብት  ለማጎናጸፍ ይተጋል። እየታገለ ያለው የኦሮሞ ህዝብ በአቢሲኒያ ቅኝ ገዥዎች ያጣውን መብት፣ ነፃነት እና ዲሞክራሲን ለማስከበር ነው። ኦነግ የህዝቡን ሉዓላዊነት ለማስከበር እና የሀገር ባለቤትነት ስሜቱን ለመመለስ እንዲሁም የኦሮሞ ህዝብ ካለ ማንም ጣልቃ ገብነት በራሱ ጉዳይ ላይ ውሳኝ ኢንድሆን እየታገለ ያለ ግንባር ነው። ኦነግ ለኦሮሞ ህዝብ የነጻነት፣ የፍትህ፣ የመብት እና ዲሞክራሲ የሚረጋገጠው ህዝቡ የራሱን እድል በራስ የመወሰን መብቱ ሲከበርለት ቢቻ እንደሆነ በጽኑ ያምናል። የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብትን የሚያደናቅፍ ማንኛውም ሁኔታ እና ተግባር የህዝቡ የህልውና ስጋት ነዉ ብሎ ይወሰዳል።

የኢትዮጵያ ኢምፓየር መንግስት ከመቶ አመት በላይ የኦሮሞን ህዝብ ቋንቋ፣ ባህል፣ የአስተዳደር ስርዓት እና ሃብት ንብረቱን ለማስወገድ/ለማውደም የሚችለውን ሁሉ አድርጓል። የኦሮሞ ህዝብ እንደማንኛውም አፍሪካዊ ሀገር በቅኝ ገዥዎቹ ሲሰቃይ የኖረ ትልቅ ህዝብ ነው። የኢትዮጵያ ኢምፓየር የተመሰረተችው የኦሮሞን ህዝብ በማስገበር እና በሀገሩ ላይ ባርያ  በማድረግ ነው። በዚህ የጨቋኞች አገዛዝ ስር የኦሮሞ የአባቶች እጆችቻቸዉን ተቆርጠዋል; እናቶች ጡቶቻቸዉን ተቆርጠዋል; የኦሮሞ ወንዶች እና ሴቶች እንደ ቤት እንስሳት ይሸጡ ነበር፤መሬታቸው ተዘርፏል እንዲሁም መላዉ ሃገራቸው። ይህ ሁሉ ሳያንስ  ከሰብአዊነት በታች ተዋርደዋል; እናም ጋላ የሚባል አዋራጅ ስም ተሰቷቸው ነበር። በቅኝ ገዛት ስር በነበሩ የአፍሪካ ሀገራት ላይ የተፈፀመው አረመኔያዊ ድርጊት በኦሮሞ ህዝብ ላይ እና በኦሮምያም ምናልባትም በከፋ መልኩ ተፈጽሟል።

ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ኢምፓየር ኦሮሞን ለማጥፋት ያላለሰለሰ ጥረት ቢታደርግም፣የኦሮሞ ህዝብ ማኅበራዊ፣ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሀብቱን ለማስመለስ በተከታታይ የነበሩ አምባገነን መንግስታትን በመታገል እና በመቋቋም ህልማቸዉን ማምክን ችሏል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የመጨረሻዎቹ አስርት አመታት በአቢሲኒያውያን ቅኝ ግዛት ስር ከወደቀ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሃገር የመመስረት ጽኑ ፍላጎቱን በትግሉ አሳዪቷል። የኦሮሞ ህዝብ ከቅኝ ገዥ ሃይሎች ጋር በተለያየ መልኩና መንገድ ሲያድርግ የነበርዉን ትግል ለአፍታም አላቆመም።

የጠራ የፖለቲካ ዓላማና ራዕይ ያለው ይበልጥ የተደራጀ የፓን-ኦሮሞ ትግል የተጀመረው በ1973 የኦነግን መቋቋም ተከትሎ ነው ። የኢትዮጵያ ኢምፓየር  በኦሮሞ ትግል እና የተማሪዎቹ “Land to the Tillers” በሚል መሪ ቃል እንቅስቃሴ  በ1974 እኢአ ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ውድቀት ጋር ከስሟል። ይሁን እንጂ የኢምፓየር ግዛት የጠፋ ቢሆንም፣ የኢምፓሩ ተፈጥሮአዊ ባህሪያት ግን እስከ ዛሬ ድረስ እየኖሩ ጉዳት ማድረሳቸዉ ቀጥሏል።

በኦሮሞ ነጻነት ግንባር የሚመራው የኦሮሞ ህዝብ ትግል የመጨረሻ የፖለቲካ አላማውን አሁንም አላሳካም። ይሁን እንጂ በ50ኛው የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል የሚከበሩ እጂግ ደማቅ ድሎች አሉ። ከነዚህም መካከል ጥቅቶቹ፤

/ የኦሮሞ አንድነት፡ ኦነግ ኦሮሞ በቅኝ ገዢዎች ስር በጎሳ፣ በጂኦግራፊያዊ አሰፋፈር፣ በኃይማኖት እና ወዘተ ተከፋፍሎ የነበረዉን እልህ አስጭራሽ ትግል በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድነቱን ማስመለስ ችሏል። ኦነግ ህዝቡ የሃይማኖት፣ የጂኦግራፊያዊ አሰፋፈር እና ሌሎች ሁኔታዎች ሳይገድቡት መላውን ኦሮሞ የሚያቅፍ እና የጋራ ማንነት ያለው ኦሮሙማን ለመገንባት በማያሻማ መልኩ ታግሎ አሳክቷል። ሁሉም ሰማዕቶቻችን በተለይ በሺኒጋ የተሰዉት አንድነታችንን አጠንክረው ከአሁን በኋላ ማንም ኃይል ሊከፋፍለን በማይችል መልኩ በጽኑ አለት ላይ ተክለው ለዘላለም አልፈዋል።

/ የኦሮሚያ ክልል፡ ኦሮሚያ በሕዝብ ብዛትም ሆነ በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ አንዳና ትልቋ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ  አባል  መሆኗ ታውቋል፡፡ይሁን እንጂ  እስካሁን ድረስ ያልተረጋገጡ እና እልባት ያላገኙ የክልሉ የድንበር ይገባኛል ጥያቄዎች መኖራቸው ይታወቃል። ዛሬ የኦሮሞ ህዝብ እና ኦሮምያ በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ የሚታወቅ እና ተሰሚነት ያለው ሆኖ ይገኛል፡፡

/ ኦሮምኛ ቋንቋ፡ አፋን ኦሮሞ በትምህርት ቤቶች የመገናኛ ዘዴ እና በኦሮምያ ብሔራዊ ክልል ውስጥ የስራ ቋንቋ በመሆን እያገለገለ ይገኛል። ምንም እንኳን የፓለቲካው ሁነታ ያልተመቻቸ ቢሆንም  በአፋን ኦሮሞ ጋዜጦች፣ መጽሔቶች፣ ታሪኮች፣ ልቦለዶች እና ልዩ ልዩ መጻሕፍቶች በየጊዘው እየታተሙ ይገኛሉ፡፡

/ የኦሮሞ ባህል፡ አብዮት እስኪ መስል ድረስ የባህል ተሀድሶዎች ተካሂደዋል። የኢሬቻ በዓል አከባበር (ባህላዊው የምስጋና ሥነ ሥርዓት) በአሁኑ ጊዜ በኦሮሚያ ትልቁ በዓል እየሆነ ነው። የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ስርዓትን (ገዳ) መልሶ ለመገንባት የተደረገው ሙከራ ምንም እንኳን ቀሪ ስራዎች ቢኖሩትም ጉልህ ስኬቶችን አሳይቷል። የኦሮምያ የባህል አልባሳትና ምግቦች ለገበያ እየቀረቡ በኦሮምያና ከዚያም አልፎ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ይግኛል።

/ ኦሮሞ ስነ ጥበብ/አርትስ፡ የኦሮምኛ ሙዚቃ ኢንዱስትሪ በፍጥነት እያደገ ነው። የኦሮሚኛ ሙዚቃ የኦሮሞን ህዝብ ለነጻነት እና ለዲሞክራሲ ትግል በማነሳሳት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የኦሮሞን ባህል በማሳየት ላይ ያለው ትልቅ ሚና በአለም ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ መጥቷል። የኦሮሞ ድራማ፣ ቲያትር እና የፊልም ኢንዱስትሪዎች ገና ተቋማዊ ባይሆኑም ተስፋ ሰጭ እና በማይቀለበስበት ደረጃ እያደጉ ናቸው።

/ የኦሮሞ በራስ መተማመንን ማጎልበት፡ አብዛኛው አዲሱ ትውልድ ኦሮሞ የሚጠራው በኦሮሞ ስም ነው እና ኦሮሞ ስለመሆኑ የሚኮራበት ነው። የራሳቸውን ማንነት ከማንሰራራት አንፃር  በአዲሱ (ቁቤ) ትውልድና በቀደሙት  ትውልዶች መካከል ጉልህ የሆነ ልዩነት ይታያል; እና

/ አለም አቀፍ ዲፕሎማሲ፡ ምንም እንኳን ኦነግ በ ዲፒሎማሲዉ መስክ ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለኦነግ የፖለቲካ አጀንዳ ለአስርት አመታት ተገቢዉን ኢውቅና ነፍገውታል። በአሁኑ ጊዜ ግን የኦነግ የፖለቲካ አጀንዳዎች ሰፊ እውቅናና ትኩረት አግኝቷል፡፡ ያለ ኦነግ ተሳትፎ በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የፖለቲካ መረጋጋት ሊመጣ እንደማይችልም እየታወቀ መጥቷል።

እነዚህ ድሎች የከፍተኛ መስዋዕትነት ዉጤት ናቸው። በዚህ የ50 አመት የትግል ጉዞ ኦሮሞ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወንዶች እና ሴቶቸ ጀግኖችን  አጥቷል።  ኤሌሞ ቅልቱ፣ ታደሰ ብሩ፣ ባሮ ቱምሳ፣ ማጋርሳ ባሪ፣ ጃራ አባ ገዳ፣ ባdho ዳቻስ፣ ገዳ ገመዳ፣ አቦማ ምትኩ፣ ይገዙ በንቲ፣ ሙሄ አብዶ፣ ነdhi ገመዳ፣ ጋማቺስ Dhaባ፣ ቡሩይሶ ቦሩ፣ ሚልኬሳ ​​ጋዳ፣ ጉተማ ሃዋስ፣ ናጋሳ ኩምሳ ጉቱ ጫሊ, ለገሰ ወጊ የነፃነት እና የዲሞክራሲን መንገድ ለመዘርጋት ከፍተኛ መስዋዕትነት ከከፈሉ የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ወንድና ሴት ልጆች ያለ ህጋዊ አሰራር በተለያዩ እስር ቤቶች እና ማጎሪያ ማዕከሎች ተንገላተዉበታል። ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ህይወታቸውን ለማትረፍ ከአገሪቱ ወደ አፍሪካ፣ አውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ ሀገራት እና ሌሎችም ተሰደዋል።

የ1980ዎቹ በኦጋዴን ሺኒጋ  የኦነግ ልዑካን ላይ የተፈጸመው ግድያ  የኦሮሞን ህዝብ አንድነት ለማረጋገጥ ጠንካራ መሰረትን የጣለ ነበር። ከሃይማኖታዊ አስተምህሮዎች የተነሳ የኦሮሞ ህዝብን በሃይል ማከፋፈል ከሰማዕቶቻችን አስከሬን ጋር ዳግም ላይነሳ ተቀበሯል። ሰማዕታቶቻችን በትውልድ የሚዘከሩ ታሪካዊና የኦሮሞ አንድነት ልዩ ምልክቶች ሆነው ይታወሳሉ። በ1991 እና 2018 እ.ኤ.አ. የኢትዮጵያ ኢምፓየርን ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማሸጋገር ከ የኦነግ ጋር የተደረጉት ድርድሮች እና ስምምነቶች ለዉጥን ከመሻት ይልቅ ግንባሩን ለማጥፋት የታለመ እኩይ ተግባር ሆነው አልፈዋል። በሁለቱም ጊዜያት ኦነግ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ታጣቂ ሃይሎችን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ወጣቶችን (ቄሮ/ቃሬሬ) አጥቷል። ባለፉት 50 ዓመታት የኦነግ የነጻነት ታጋዮች  ባለማቋረጥ የመጨረሻውን መስዋዕትነት ስከፍሉ ቆዪተዋል። ኦነግ የተመሰረተበትን 50ኛ አመት የምስረታ በዓል ስናከብር የሚታወቁ እና የማይታወቁ ሰማእቶቻችንን በማሰብ ጭምር ነው፡፡

ኦነግ የገጠሙትን ፈተናዎች ሁሉ ተቋቁሞ የህዝቦቹን ፍላጎት – የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ለማረጋገጥ አመራር መስጠቱን ቀጥሏል። ለበዓሉ አከባበር ስንዘጋጅ በአብዛኛዉ የኦሮምያ አካባቢዎች ሰላምና መረጋጋት የለም; በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና በብልጽግና ፓርቲ መንግስት ጦር መካከል ውጊያ እንደቀጠለ ነው። ንጹሐን ሰዎች ይገደላሉ; ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል; እና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ህዝብ በተለያዩ እስር ቤቶች እና ማጎሪያ ቦታዎች በህገ ወጥ መንገድ እየተሰቃዩ ይገኛሉ። የኦነግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የሆኑት አቶ አብዲ ረጋሳ እና ሚካኤል ቦራን ጨምሮ የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች እና ነባር አባላቶቻችን ያለ ህግ አግባብ  ለሶስት አመታት በእስር ላይ ይገኛሉ። ሁሉም የኦነግ ቢሮዎች በመንግስት ተዘግተዋል።

ኦነግ እነዚህን ሁሉ ተግዳሮቶች ተቋቁሞ የማይበገር እና የማይለወጥ ሆኖ ኖሯል እናም የኦሮሞን የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እስከሚያረጋግጥ ድረስ የመሪነቱን ሚና መጫወቱን ይቀጥላል። ኦነግ 50ኛ ዓመቱን በሚያከብርበት በዚህ ጊዜ፡

  • የኢትዮጵያ መንግስት እና ከዚህ መንግስት ጀርባ ያሉ የሚመለከታቸው የፓለቲካ ፓርትዎች በሙሉ በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት ኢንዲያደርጉ ጥሪ ያቀርባል። ለተባባሰው የፖለቲካ ቀውስ የመጨረሻ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት ኦነግ የበኩሉን ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል፣
  • ሰላማዊ፣ዲሞክራሲያዊ እና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ሽግግርን ለማመቻቸት ብሔራዊ የሽግግር መንግሥት በኦሮሚያ እንዲቋቋም ይሰራል፣
  • ከአጋር/እህት ድርጅቶች ጋር ያለውን አጋርነት እና ትብብር  በማጠናከር፣ እንዲሁም ተመሳሳይ የፖለቲካ አላማዎችን ከሚጋሩ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የሚመለከታቸው የሲቪክ ማህበራት ጋር በቅንጅት ይሰራል፣
  • ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ግንኙነት በመፍጠር ስለ ኦሮሞ የፖለቲካ ሁኔታ ሰፊ ግንዛቤን ለመፍጠር እና ለፍትሃዊ ዓላማ ድጋፍ እንድያደርጉ ይጠይቃል፣
  • የኦሮምያ ወጣቶች(ወንዶችና ሴቶች)ን በማደራጀትና በማስተባበር ለመብታቸው እንዲታገሉ፣ ያገኙትን ድል እንዲያስከብሩ፣ ብሎም የቀጠለውን አፈና እና ጭቆና ከላያቸዉ እንዲያስወግዱ በጽናት ይሰራል።

ድል ​​ለሰፊው ህዝብ!

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር 50ኛ ኢዮቤልዩ የምስረታ በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ

ሰኔ፣ 2023

SBO
ADMINISTRATOR
PROFILE

Posts Carousel

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

Latest Posts

Top Authors

  • SBO
    ADMINISTRATOR

Most Commented

Featured Videos

Categories

SBO