50ኛ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ምስረታ ክብረ-በዓልን ኣስመልክቶ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር የተሰጠ መግለጫ
50ኛ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ምስረታ ክብረ-በዓልን ኣስመልክቶ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር የተሰጠ መግለጫ
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ለመላው ታጋዮች፣ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ለመላው የኦሮሞ ህዝብ እንኳን ለ50ኛ ዓመት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ምስረታ ክብረ-በዓል አደረሳችሁ ይላል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በተደበላለቀ ስሜት ውስጥ ሆኖ ነው የሚያከብረው።
በአንድ በኩል የኦሮሞን ህዝብ የሃገር ባለቤትነት ለማረጋገጥ ላለፉት ለዥም ዓመታት በተደረገው ትግል ቤተሰባቸውን በትነው የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉት፣ ኣካላቸውንና ኑሮኣቸውን ያጡበት ጀግኖቻችን እንዲሁም ኣሁንም መስዋዕትነት እየከፈሉ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆችን በሃዘን ያስታውሳል። በአንፃሩ ደግሞ ጓዶቻችንና ኦሮሞ ህዝብ በተከፈለው በዚህ ክቡር መስዋዕትነት ኦሮሚያን ከመጥፋት መታደግ እንዲሁም የኦሮሞን ቋንቋና ባህል ከጥፋት ታድገን እዚህ መድረስ መቻላችንን በደስታ እንገልጻለን። እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን!
በዚህ ትግል የኦሮሞ ህዝብ የከፈለው ከባድ መስዋዕትነት በኦሮሞ ታሪክ ውስጥ ለዘልዓለም እያንጸባረቀ ከትውልድ ወደ ትውልድ ተላልፎ የሚገባውን ክብር እንደሚያገኝ ሙሉ እምነታችን ነው። የኦሮሞ ህዝብ ውድ መስዋዕትነት የከፈሉትንናስ በመክፈል ላይ የሚገኙትን ጀግኖቹን እየዘከረ፡ ነጻነቱን እና የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብቱን በእጁ እስከሚያስገባ ድረስ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ከፍሎ ይህን እውነቱንና መንብቱን መጎናጸፍ ኣለበት። ባለፉት ዓመታት በትግሉ የተመዘገቡት ውጤቶች ከንቱ አይደሉም።
ባለፉት ለዝጅም የትግሉ ዓመታት ያሳለፍናቸው ውጣ ውረዶች ቀላል ኣይደሉም። የተቀሩትን መብቶቻችንን ለማስከበር የሚጠብቀን ትግልም እንዲሁ ቀላል አይሆንም። የኦሮሞ ህዝብ በኣካልና በሃብቱ ከኦሮሞ የነጻነት ትግል መሪ ድርጅት፡ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጎን በመሰለፍ የተነፈገውን ፍትህና መብቱን ሙሉ በሙሉ ለማስከበር አስፈላጊውን ጥረት ማድረግ አለበት።
ይህንን በዓል ስናከብር በመላው ኦሮሚያ ሊባል በሚችል ደረጃ ሰላም ደፍርሶ፣ የመንግስት መዋቅር ፈርሶ፣ ህዝቡ ከመንግስት ማግኘት የሚገባውን አገልግሎት ባግኘት በማይችልበትድ ሁኔታ ላይ ይገኛል። በመላው ኦሮሚያ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ከቀያቸው አፈናቅሏል። በሰላም ወጥቶ መግባት በእጅጉ አሳሳቢ ነው። ወቅቱን የጠበቀ ዝናብ ባለመኖሩ ለረሃብ ተጋልጠው የነበረው ህዝብ ቁጥሩ ጥቂት የሚባል ኣይደለም። የዋጋ ግሽበቱ በገጠርና በከተማ ኑሮውን የከፋ አድርጎታል። በሀገሪቱ ያለው ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ ነው። በወቅቱ መፍትሄዎች ካልተፈለገ በስተቀር ሊደርስ የሚችለው ጉዳት በጣም ያሳስባል።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) የነዚህ ችግሮች ዋነኛ መንስኤ የኦሮሞን የፖለቲካ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ለመመለስ ካለመፈለግ የመነጨ ነው ብሎ ያምናል። ጥያቄዎቹ ምላሽ ኣግኘተው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ህዝባችን በሚችለው መንገድ ሁሉ ግፊት ማድረግ ይጠበቅበታል። ይህን ማድረግ ብቻ ለኦሮሞ ህዝብና ለኦሮሚያ ዜጎች ሰላምና መረጋጋትን ያረጋግጣል ብለን እናምናለን።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እየተፈረካከሰ ያለው የኦሮሚያ መንግስት መዋቅር ተጨማሪ ኣደጋ ሳያስከትል የህግ የበላይነት ተከብሮ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር በማሰብ; የኦሮሚያ ክልል ብሄራዊ የሽግግር መንግስት በማቋቋም ላይ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ሥራ ላይ የተሰማሩትም የኦነግን ሃሳብ ኣንግበው እየተጓዙ ስለሆነ አስፈላጊ እና ወሳኝ መሆኑን መሆኑን እናምናለን። የኦሮሞ ህዝብ በዚህ ረገድ ያለውን ሁኔታ በጥልቀት ተረድቶ ተጨማሪ ያልተገቡ ችግሮችን ለማስወገድ የኦሮሚያ ክልል ብሄራዊ የሽግግር መንግስትን መደገፍና ማጠናከር አለበት። የህግ የበላይነት ከተረጋገጠና መልካም አስተዳደር ካለ ዘላቂ ሰላም ሊኖር ይችላል። የኦሮሞ ህዝብና የኦሮሚያ ዜጎች እየተገነባ ያለውን የኦሮሚያ ክልል ብሄራዊ የሽግግር መንግስት ለማጽናት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው እንረዳለን።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ዛሬም እንደትላንቱ የኦሮሞን ህዝብ የራስን እድል በራስ የመወሰንና የሃገር ባለቤትነት መብት ለማስከበርና የዲሞክራሲ ስርዓትን ለማስፈን የሚያደርገውን ትግል በቁርጠኝነት አጠናክሮ ይቀጥላል። ቀደም ሲል ውድ መስዋዕትነት ከፍሎ የኦሮሞን ህዝብ ትግል ከዛሬ እንዳደረሰው ሁሉ ለወደፊትም ህዝባዊ ድጋፍ ያለውን ሁሉን አቀፍ ትግሉን ለማሳካት አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ለመሆኑንም በድጋሚ ቃሉን ያድሳል።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው የኦሮሞ ድርጅቶችና መብቶቻቸውን ለማስከበር ከሚታገሉ የብሄር ብሄረሰቦች ድርጅቶች ጋር ያለውን የትብብር ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮ ይቀጥላል። እንዲሁም ለዴሞክራሲያዊ መብቶችና ለሕዝቡ ሰላም መረጋገጥ ከሚታገሉ ድርጅቶች ጋር ያለውን ግንኙነትም ይበልጥ እያጠናከረ፡ ከሌሎቹም ጋር ግንኙነት ይፈጥራል። በተመሳሳይ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ያለንን ግንኙነትም የበለጠ ለማጠናከር በጥልቀት የምንሰራበት ይሆናል።
በመጨረሻም፡ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ረጅም ዓመታታን በወሰደውና በሺዎች የሚቆጠሩ ጀግኖችን መስዋዕትነት ኣስከፍሎ ከዛሬ የደረሰውን ትግል 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ሲያከብር ለትግሉ የገባውን ቃል በድጋሚ እያደሰና ኣስፈላጊውን መስዋዕትነት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ መሆናችንን እየገለጽን ይህ 50ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ-በዓል የስኬት እንዲሆን እንመኛለን።
ድል ለሰፊው ህዝብ!
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
ሰኔ 30 ቀን 2023ዓም
ፊንፊኔ



Sagalee Bilisummaa Oromoo














Leave a Comment
Your email address will not be published. Required fields are marked with *