በኦሮሚያ ስለደረሰው አሰቃቂ ጥቃት መግለጫ የኦሮሚያ ተሟጋች ድርጅት (አድቮኬሲ ፎር ኦሮሚያ) በመንግስት እየተደገፈ ያለውን ሁከት እን ብጥብጥ በማያሻማ መልኩ ያወግዛል፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰብአዊነት ላይ ወንጀል የፈፀመውን የታጠቀ የፋኖ ሚሊሻ ማሰማራቱን፣ በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ የሰው አልባ አውሮፕላን የቦምብ ጥቃትና የአየር ድብደባ ያወግዛል። ይህ እርምጃ የጅምላ ጭፍጨፋዎችን፣ መፈናቀልን እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰብዓዊ ድንገተኛ አደጋዎችን
በኦሮሚያ ስለደረሰው አሰቃቂ ጥቃት መግለጫ
የኦሮሚያ ተሟጋች ድርጅት (አድቮኬሲ ፎር ኦሮሚያ) በመንግስት እየተደገፈ ያለውን ሁከት እን ብጥብጥ በማያሻማ መልኩ ያወግዛል፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰብአዊነት ላይ ወንጀል የፈፀመውን የታጠቀ የፋኖ ሚሊሻ ማሰማራቱን፣ በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ የሰው አልባ አውሮፕላን የቦምብ ጥቃትና የአየር ድብደባ ያወግዛል። ይህ እርምጃ የጅምላ ጭፍጨፋዎችን፣ መፈናቀልን እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰብዓዊ ድንገተኛ አደጋዎችን አስከትሏል።
ኦሮሚያ ከ1900ዎቹ መጀምሪያ ጀምሮ በኢትዮጵያ ባርነት ስር ነች። የኦሮሞ ህዝብ በኃይል የተነጠቃዉን ሰብአዊ መብት ለማስመለስ ያልተቋረጠ ትግል ሲያደርግ ቆይቷል። በዚህ ወቅት የ1974፣ 1990 እና 2018 መልካም እድል በኢትዮጵያ መንግስታት ግትርነት ከሽፏል።
ምንም እንኳን ኦሮሞ ሰላምን የሚወድ እና በሰላም እና በነጻነት ለመኖር ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖረውም, እነዚህ ፍላጎቶች አልተሟሉም። ይልቁንም ሁኔታው በብዙ መልኩ እየተባባሰ ነው። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት መሳሪያ ባልታጠቁ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና የአየር ድብደባዎችን በማድረግ በርካታ ንብረቶችን እያወደመ ነው። በመንግስት የሚደገፈው የአማራ ሚሊሻ (ፋኖ) ታጣቂ ሃይሎችም ወደ ተለያዩ የኦሮሚያ ቦታዎች በመግባት የህዝቡን አንገት እየቆረጡ እና ዛፍ ላይ ሰቅለው እየዘፈኑባቸው ነው።የንፁሃንን ሕይወት መቅጠፍ እና ይህን አረሜኒያዊ ድርጊት ቀርጾ ለዜጎች ማስተላለፍም ቀጥሏል። የዚህ ዘግናኝ ድርግት ዓላማም ሰዎች ፍርሃት ውስጥ እንዲገቡ እና እንዲደናገጡ ማድረግ መሆኑ ግልጽ ነው። የህዝብ ንብረት መዝረፍና ማቃጠል ቀጥሏል።
በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል; ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እየታገዱ ጊዜያቸው እየባከነ ነው። በኦሮሚያ እየተካሄደ ያለው ያልተቋረጠ ሁከትና ግጭት የኦሮሞን ህዝብ ህይወትና ኑሮ እያወደመ ነው; የኦሮሞ ቤተሰቦችን እየፈረሰ ነው; ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ አስከፊ የስሜት ቀውስ እየፈጠረ ነው።
ኦሮምያ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ህገ-ወጥነት እና ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እየታየ ነው። በብዙ የሀገሪቱ ክፍሎች ቀልጣፋ የፍርድ ቤት ሥርዓት ባለመኖሩ የዜጎች ስቃይ፣ ሰቆቃ እና ሞት ለፍርድ አይቀርቡም።
የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ትኩረት ባለማግኘታቸው በደርዘን የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች በእስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ። በቅርቡ በተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ ኮንግረስ ስብሰባ በኦሮሚያ የተፈጠረውን ግጭት በወታደራዊ ሃይል ለመፍታት መወሰኑ በጣም አሳሳቢ ነው። ጉዳዩን የበለጠ የከፋ ያደርገዋል። እናም ሰላማዊ ድርድር እንዲደረግ ግፊት ማድረግ አስፈላጊ ነው።
በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ እየደረሰ ያለውን ጥቃትና ሰቆቃ በዘላቂነት ለመፍታት በአገር ውስጥና በውጪ ከፍተኛ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው። በመሆኑም፣ በሁሉም ድምጽዎ እና ችሎታዎ:
1. በኦሮሚያ የተፈጠረውን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ ድርድር እንዲፈታ የኢትዮጵያ መንግስት ግፊት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን።
2. የአውስትራሊያ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብር እና እንዲያስከብር ሁሉንም ድምጽ እንዲጠቀም እናሳስባለን።
3. የአውስትራሊያ መንግስት በኦሮሚያ ውስጥ የተፈፀመውን አንገት የመቅላት፣ ግድያ እና ዘረፋ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት እናሳስባለን።
4. ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ሰብአዊ እርዳታ እንዲያደርግ እንጠይቃለን።
5. በአጎራባች ሀገር ለሚኖሩ የኦሮሞ ስደተኞች ደህንነት ደጋፍ እና ጥበቃ እንዲደረግ በማንኛውም መንገድ ለአለም መንግስታት እንድትደውሉ እና እንዲታሳውቁ በትህትና እንጠይቃለን።
ጥብቅና ለኦሮሚያ
ታህሳስ 10 ቀን 2022

Sagalee Bilisummaa Oromoo














Leave a Comment
Your email address will not be published. Required fields are marked with *