The Amhara/Fano armed forces attacked the Oromo citizens of Wollo and killed more than 44 innocent people in the past three days.
News Update: In North Sheger Zone, Showa Robit area and in North Oromia Hartuma Furse district of Wollo zone 44 innocent Oromos were killed.

[Voice of Oromo Liberation (SBO) January 23, 2023] The armed forces of the Amhara region continue the mass killings of peaceful Oromo citizens. Today, January 23, 2023, in a place called Kere-Jejaba near Showa Robit, the news reached us that after looking at their identity cards, Oromo civilians were taken out of a car and killed. It explains. Among those killed was Sheikh Amin Aliyi Sheikh Muhammad, a prominent Oromo nationalist. Kere-Jejaba is a place on the border between Shawa Robit and Jile Dumuga.
Starting from January 21, 2023, Amhara region militants and Fano forces armed with heavy weapons are jointly attacking the Oromo people in the Wolo zone of North Oromia. The Amhara/Fano militants attacked the Oromo people in Jile-Dumuga district of Wolo Zone, Hataye, Guba-Wachu, Halale, Dirich, Kundae, Marare, Jawaha, Negeso, Balchi, wesen-Kukur and Kare-Jejeba kebeles as well as Sembete district and killed several Oromo civilians.
In the same way, on January 21st, 2023, in the Harwacha area of Hartuma Furse district, Amhara terrorist forces killed 7 people and wounded 12 others. Today, January 23rd, 2023, these Amhara armed forces killed 21 people in their attack on unarmed civilian people, and it is known that they are burning and destroying the people’s homes and their property.
The Amhara/Fano armed forces attacked the Oromo citizens of Wollo and killed more than 44 innocent people in the past three days.
===================================================
አሁን የደረሰን ዜና
በሰሜን ሸገር ሸዋ ሮቢት ኣካባቢ 16 እንዲሁም በወሎ ዞን ሃርክሱማ ፉርሴ ወረዳ 28 ንጹሃን የኦሮሞ ተወላጆች ተገደሉ።
[የኦሮሞ ነጻነት ድምጽ (SBO) ጥር 23, 2023ዓም፡] የአማራ ክልል ታጣቂ ሃይሎች በሰላማዊ የኦሮም ዜጎች ላይ የሚፈጽሙትን የጅምላ ግድያ በመቀጠል፡ ዛሬ ጥር 23, 2023ዓም ሸዋ ሮቢት አቅራቢያ በምትገኘውና ከረ-ጀጀባ በተባለ ቦታ ሰላማዊ የኦሮሞ ዜጎችን የመታወቂያ ወረቀታቸውን የተመለከቱ በኋላ ከመኪና ኣውርደው እንደገደሏቸው የደረሰን ዜና ይገልጻል። ከተገደሉት መካከል ሼክ አሚን አሊዪ ሼክ ሙሀመድ የተባሉ ታዋቂው የኦሮሞ ብሄርተኛ ይገኙበታል። ከረ-ጀጀባ በሸዋ ሮቢት እና በጂሌ ዱሙጋ ድንበር ላይ የሚገኝ ቦታ ነው።
ከጥር 21 ቀን 2023 ጀምሮ ከባድ መሳሪያ የታጠቁ የአማራ ክልል ታጣቂዎች እና የፋኖ ሃይል በጋራ በመሆን በሰሜን ኦሮሚያ ወሎ ዞን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጥቃት በመፈጸም ላይ ይገኛሉ። በወሎ ዞን ጂሌ-ዱሙጋ ወረዳ ውስጥ በሃጣዬ፣ ጉባ-ዋጩ፣ ሃላለ፣ ዲሪጭ፣ ኩንዴ፣ ማረሬ፣ ጃዋሃ፣ ነጌሶ፣ ባልጪ፣ ወሰን ቁቁር እና ካረ-ጀጀባ በተባሉት ቀበሌዎች እንዲሁም በሰምበቴ ወረዳ የአማራ/ፋኖ ታጣቂዎች በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጥቃት በመሰንዘር አያሌ ሰላማዊ ዜጎችን ገድለዋል።
በተመሳሳይ መልኩ ጥር 21 ቀን 2023ዓም በሃርጡማ ፉርሴ ወረዳ ሃረዋጫ በተባለ ቦታ የአማራ አሸባሪ ሃይሎች በኦሮሞ ህዝብ ላይ በፈጸሙት ጥቃት 7 ሰዎችን ሲገደሉ 12ቱን ደግሞ ማቁሰላቸን የደረሰን ዘገባ ያለመክታል።
ዛሬ ጥር 23, 2023ዓም እነዚሁ የአማራ ታጣቂ ሃይሎች የመሳሪያ-ኣልባ ህዝብ ላይ በፈጸሙት ጥቃት 21 ሰዎችን የገደሉ ሲሆን የህዝቡን መኖሪያ ቤቶችም ከነንብረታቸው እያቃጠሉና እያወደሙም መሆኑ ታውቋል። የአማራ/ፋኖ ታጣቂ ሃይሎች በወሎ የኦሮሞ ዜጎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት በሶስት ቀናት ውስጥ ከ44 በላይ ንፁሃን ዜጎች ህይወት ተቀጥፏል።
Sagalee Bilisummaa Oromoo














Leave a Comment
Your email address will not be published. Required fields are marked with *